- የማኀበራዊ አገልግሎት
በቤተክርስቲያን አባላት መካከል የማኀበራዊ አንድነት መጠበቅ፡- እንዲሁም በማኀበራዊ አገልግሎት ተሣትፎ እንዲያደርጉ በማትጋት ከመንፈሳዊ አገልግሎትዋ ሌላ የማኀበራዊ አገልግሎትም ታካሂዳለች፡፡ ማኀበራዊ አገልግሎቱ የሚተዳደርበት የራሱ የአሠራር መመሪያ ያለው ሲሆን በሚከተሉት ማኀበራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል፡፡
- የቤተክርስቲያኑ አባላት ደስታና ሐዘን ሲያጋጥማቸው በሚያስፈልጋቸው ማኀበራዊ ሁኔታዎች በመካፈል ረገድ አባላትን ያስተባብራል፡፡
- የጋራ የሆነ የማነቃቂያ የሪትርት ኘሮግራም ሲካሄድ፣ ሌሎችም ማኀበራዊ ዕቅዶች ሲዘጋጁ፣ በእነዚህ ሁሉ እንዲሳተፉ ያስችላቸዋል፡፡