• የቤተክርስቲያኑ አመራር/አስተዳደር
• ቤተክርስቲያኑ ራሱን በራሱ የሚመራበት መተዳደሪያ ደንብና የውስጥ ደንብ አለው፡፡ በመተዳደሪያ ደንቡ መሠረት፡- ቤተክርስቲያኑ በሽማግሌዎች የሚመራ ሲሆን፣ አመራሩም “የሽማግሌዎች አስተዳደር አካል” በመባል ይታወቃል፡፡ መንፈሣዊ አስተዳደር ለውጤታማ የቤተክርስቲየን ዕድገት ጠቃሚ ስለሆነ፣ እግዚአብሔር በሰጣቸው ሥጦታና ዕውቀት ቤተክርስቲያኑን የሚያስተዳድሩ የአመራር አካላት አሉት፡፡ እነዚህም በመተዳደሪያ ደንቡና በመዋቅሩ መሠረት በየሁለት ዓመቱ በአባላት ጠቅላላ ጉባዔ ይመረጣሉ፡፡